ተወጥቶ ተወርዶ የትም ሀገር ቢኖር፣
አገርቤትም ሆነ ከባህር ባሻገር፣
ጉድለት አለ ሲባል ሥሰማ ሲነገር፣
ብዙ ያገሬ ሰው ቃሉን ሳያከብር፣
እቅድ ሳያወጣ ባጋጣሚ መኖር፣
እንዲህ የገነነ አይመስለኝም ነበር፡፡
ስማችን አይጥፋ በቀጠሮ ምክንያት፣
እስኪ በቃ ብለን ዛሬ እንነሳበት፣
በሰዓቱ እንድረስ ቃል ለገባንለት፣
ቶሎ ሳንዘገይ በተባለው ሰዓት፣
ከዛ ከተባለው ቦታ ለመገኘት፣
ለቀጠርነውም ሰው ክብር ለማሳዬት፣
በደንብ ተገንዝበን የቀጠሮን ክብዴት።
በሰዓቱ መድረስ እንደምን አቃተን?
እስከመቼ ድረስ ሁልጊዜ ዘግይተን፣
በትንሿ ነገር ካልተለማመድን?
ነጻነትና እድገት መቼ እናገኛለን?
Error: No site found with the domain 'mail.mejemer.com' (Learn more)